የአማራ ክልል ዳኞች ማኅበር የሕፃን ሔቨን ይግባኝ በፍርድ ቤት መታየት ዳኞች ሕግን መሠረት አድርገው "በነፃነት እንዳይሠሩ ያልተገባ ጫና" ያሳድራል ሲል ተቃውሞ አሰማ

በሕፃን ሔቨን ላይ የአስገድዶ መድፈር ወንጀል ፈጽሞ ለሕልፈት በመዳረግ የ25 ዓመት ጽኑ እሥራት የተፈረደበት ጌትነት ባይህ ያቀረበውን ይግባኝ ፍርድ ቤቱ በማየቱ የተጀመረውን የተቃውሞ ዘመቻ የአማራ ክልል ዳኞች ማኅበር አውግዟል።

Heaven A.png

Heaven Credit: PD

ማኅበሩ፣ የሴቶችና ማኅበራዊ ጉዳይ ሚንስቴርና ማኅበራዊ መገናኛ ዘዴዎች የሚያካሂዱት ዘመቻ ከዳኝነት ነፃነትና ከሕግ የበላይነት መርህ ያፈነገጠና ዳኞች ሕግን መሠረት አድርገው "በነፃነት እንዳይሠሩ ያልተገባ ጫና" እንደሚፈጥር ገልጧል።

በአገሪቱ ሕግ በወንጀልም ኾነ በፍትሐብሄር የተፈረደበት ወገን ይግባኝ የመጠየቅ ሕገመንግሥታዊ መብት እንዳለው የጠቀሰው ማኅበሩ፣ ግለሰቡ ይግባኝ ማቅረብ የለበትም የሚል ዘመቻ ማድረግ "በሕግ የመዳኘት መብትን አደጋ ላይ የሚጥል" እና በፍርድ ቤቱ ላይ "ያልተገባ ጫና በማሳደር የዜጎችን ፍትሕ የማግኘት መብት" ይጥሳል ብሏል።

ሚንስቴሩ ይግባኝ መቅረቡን ተቃውሞ በጉዳዩ ላይ ከባለድርሻ አካላት ጋር እንደሚሠራ መግለጡ ይታወሳል።


Share
Published 19 August 2024 3:16pm
Updated 19 August 2024 3:23pm
By Stringer Report
Source: SBS

Share this with family and friends


Follow SBS Amharic

Download our apps
SBS Audio
SBS On Demand

Listen to our podcasts
Independent news and stories connecting you to life in Australia and Amharic-speaking Australians.
Ease into the English language and Australian culture. We make learning English convenient, fun and practical.
Get the latest with our exclusive in-language podcasts on your favourite podcast apps.

Watch on SBS
SBS World News

SBS World News

Take a global view with Australia's most comprehensive world news service