የተወሰኑ የአማራ ክልል ክፍሎችን አካትቶ የኢትዮጵያ የፀጥታ ሁኔታ ተለዋዋጭ በመሆኑ የአውስትራሊያ መንግሥት ለዜጎቹ የጉዞ ማስጠንቀቂያ ሰጠ

የጉዞ ደኅንነት ማሳሰቢያው አዲስ አበባና ማዕከላዊ ኢትዮጵያንም ያካትታል

Passengers.jpg

Passengers wait at a Qantas departure gate in Sydney, Australia. Credit: Ryan Pierse/Getty Images

የአውስትራሊያ መንግሥት ወደ ኢትዮጵያ ለሚጓዙ ወይም በአሁኑ ወቅት ኢትዮጵያ ውስጥ ለሚገኙ ዜጎቹ የጉዞ ማስጠንቀቂያና የደኅንነት ማሳሰቢያ አውጥቷል።

ከወርኅ ማርች መጀመሪያ እስከ ዛሬ ማርች 13 ድረስ ፀንቶ ባለው ማስጠንቀቂያ መሠረት፤

አውስትራሊያውያን፤

  • በሱዳን፣ ኤርትራ፣ ኬንያ፣ ደቡብ ሱዳን ወይም በጋምቤላ ክልልና በደቡባዊ ሶማሌ ክልል ድንበሮች አካባቢ፣
  • የትግራይ ክልልና ሰሜናዊ የአማራ ክልል አካባቢዎችና የትግራይ አዋሳኝ የአፋር ክልል፣
  • በኦሮሚያ ክልል ምሥራቅና ምዕራብ ወለጋ እንዲሁም ቤንሻጉል ጉምዝ ክልል፣
  • ከጂቡቲ ጋር ዓለም አቀፍ ድንበር ከሚጋሩት በስተቀር በሌሎች ዓለም አቀፍ ድንበር ተጋሪ አካባቢዎች እንዳይጓዙ አስጠንቅቋል።
በአዲስ አበባና ማዕከላዊ ኢትዮጵያ የሚዘዋወሩ ዜጎች ከፍ ያለ ጥንቃቄ እንዲያደርጉም አሳስቧል።

የአውሮፕላን በረራዎች ወደ ትግራይ መቀጠላቸውን ያነሳው የደኅንነት ማሳሰቢያ፤ የኢትዮጵያ የፀጥታ ሁኔታ ተለዋዋጭ በመሆኑ መንገዶች በማናቸውም ጊዜያት ሊዘጉ እንደሚችሉ አመላክቷል።

አያይዞም፤

  • አሸባሪዎች ኢትዮጵያ ላይ ጥቃቶችን ሊሰነዝሩ እንደሚችሉ ሪፖርት መደረጉን ጠቅሶ፤ ጥቃቶቹ በአንስተኛ አለያም ያላንዳች ማስጠንቀቂያ ሊሰነዘሩ እንደሚችሉ አመልክቷል። የጥቃት ዒላማ ሊሆኑ የሚችሉትም ሆቴሎች፣ ገበያዎች፣ ሥርዓተ አምልኮ ማካሔጃ ሥፍራዎች፣ መንግሥታዊ ሕንፃዎች፣ የትራንስፖርትና አውሮፕላን ማዕከላት ሊሆኑ እንደሚችሉና በተለይም በብሔራዊ በዓላት ቀናት ዒላማ ሊሆኑ ይችላሉ ከሚባሉ ቦታዎች መገለል እንደሚገባ ጠቁሟል።
  • የአመፅ ጥቃቶች ሊፈፀሙ ይችላሉ፤ በተለይም የውጭ አገር ዜጎች ዒላማዎች ሊሆኑ ይችላሉ። በመስቀል አደባባይ፣ ሃያት ሬጄንሲ፣ ሂልተንና ሸራተን ሆቴሎች፣ የካ ኮረብታዎች/እንጦጦና ቦሌ መንገድ ላይ ወይም በምሽት ዜጎች ብቻቸውን እንዳይጓዙ መክሯል።
  • በሶማሌ ክልል ደቡባዊ ክፍሎችና በደቡብ ሱዳንና ኬንያ ድንበሮች አካባቢ የእገታ አደጋዎች ደረጃ ከፍተኛ ስለሆኑ፤ ከእኛ ምክር ውጪ እገታ ሊካሔዱባቸው በሚችሉባቸው አካባቢዎች የሚጓዙ ከሆነ ቢያንስ 'የፕሮፌሽናል ደኅንነት ምክርን' ያግኙ ብሏል።
  • በኤርትራ፣ ሱዳንና ሶማሊያ ድንበሮች አካባቢ መሬት ላይ የተጠመዱ ፈንጂዎች አደጋ ስለሚያደርሱ ዜጎች ጥንቃቄ እንዲያደርጉ አክሎ አሳቧል።

Share
Published 13 April 2023 9:49am
By Kassahun Seboqa Negewo
Source: SBS

Share this with family and friends


Follow SBS Amharic

Download our apps
SBS Audio
SBS On Demand

Listen to our podcasts
Independent news and stories connecting you to life in Australia and Amharic-speaking Australians.
Ease into the English language and Australian culture. We make learning English convenient, fun and practical.
Get the latest with our exclusive in-language podcasts on your favourite podcast apps.

Watch on SBS
SBS World News

SBS World News

Take a global view with Australia's most comprehensive world news service