በጎፋ ዞን በመሬት ናዳ ሳቢያ ሕይወታቸውን ያጡ ሰዎች ቁጥር 257 ደርሷል፤ እስከ 500 ሊደርስ እንደሚችል ስጋት አሳድሯል

ተመድ ለከፍተኛ አደጋ ተጋልጠው ያሉ 15,515 የጎፋ ዞን ገዜ ጉፋ ወረዳ አካባቢ ነዋሪዎችን ከተከታይ የመሬት ናዳ አደጋ ለመታደግ ወደ ሌላ ሥፍራ ማጓጓዝ ግድ እንደሚል አሳሰበ።

Amharic News Flash 2024.jpg

Credit: SBS Amharic

በጎፋ ዞን ገዜ ጎፋ ወረዳ ኬቾ ሻቻ ጎዝዲ ቀበሌ ነዋሪዎች ላይ በመሬት ናዳ ሳቢያ ሕይወታቸውን ያጡ ሰዎች ቁጥር በየዕለቱ እየጨመረ መጥቷል።

የአካባቢው ነዋሪዎች ለሞትና የመቁሰል አደጋ የተጋለጡት ሐምሌ 14 እና 15 ከፍተኛ ዝናብ ባስከተለው የመሬት ናዳ ነው።

የዞኑ መንግሥት ረዳት ተጠሪና የፖለቲካና የሕዝብ ግንኙነት ዘርፍ ኃላፊ፤ የአስቸኳይ አደጋ ጊዜ መልሶ መቋቋሚያ ዐቢይ ኮሚቴ ሰብሳቢ አቶ ኃብታሙ ፌተና ሐምሌ 16 በሰጡት መግለጫ የሟቾች ቁጥር 146 መሆኑ የተገለጠ ሲሆን፤ ሐምሌ 19 በአካባቢው ባለስልጣናት በተሰጠው መግለጫ መሠረት ሕይወታቸውን ያጡ ሰዎች ቁጥር 257 መድረሱ ተገልጧል።

በተጨማሪም የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የሰብዓዊ ጉዳዮች ቢሮ ከአካባቢው ባገኘው መረጃ መሠረት የሟቾች ቁጥር 500 ሊደርስ እንደሚችልና ከ15000 ሺህ በላይ የአካባቢው ነዋሪዎችን ደህንነት ከቀጣይ የመሬት ናዳ ለመታደግ ከአደጋ ወደ ራቀ ሥፍራ ማሥፈር እንደሚያሻ አሳስቧል።

ከመሬት ናዳው አደጋ የተረፉት ወ/ሮ ፀጋነሽ ኦቦሌ እንደምን ከኮረብታ አሽቆልቁሎ የመጣው የጭቃ ናዳ ከስድስት ልጆቻቸው ጋር እንደዋጣቸው ለአዣንስ ፍራንስ ፕሬስ ሲናገሩ "ልጆቼን ጨምሮ ከሌሎች ሰዎች ጋር በጭቃ ናዳው ተውጬ ነበር።

"ወንድሜ ዳዊት ጭቃው ውስጥ ገብቶ አወጣኝ። አራቱ ልጆቼ ሞቱ። ተቀበሩ" ብለዋል።

ባለቤታቸው በሕይወት መኖራቸውና አለመኖራቸው እስካሁን አልተረጋገጠም።

የኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ሐምሌ 16 በአራት ከባድ የጭነት መኪናዎች ሕይወት አዳኝ አቅርቦቶችን ይዞ በሥፍራው እንደተገኘ፣ የአካባቢው መንግሥትም ድጋፍ እየቸረ እንዳለና ዓለም አቀፍ ድርጅቶችም ትብብር በማድረግ ላይ እንደሚገኙ ተመልክቷል።





Share
Published 26 July 2024 5:21pm
By Kassahun Seboqa Negewo
Source: SBS

Share this with family and friends


Follow SBS Amharic

Download our apps
SBS Audio
SBS On Demand

Listen to our podcasts
Independent news and stories connecting you to life in Australia and Amharic-speaking Australians.
Ease into the English language and Australian culture. We make learning English convenient, fun and practical.
Get the latest with our exclusive in-language podcasts on your favourite podcast apps.

Watch on SBS
SBS World News

SBS World News

Take a global view with Australia's most comprehensive world news service