ሆ ብዬ መጣሁ ሆ ብዬ
አዲስ ዓመት ብዬ
አበባዮሆሽ ለምለም
አበባዮሆሽ ለምለም
የኔ አዲስ ዓመት እንዲህ የናፈቅኩህ
ምን ይኖርህ ይሆን አንተን የጓጓሁህ
ያለፈውስ ዓመት በምን ይገለፃል
ይለፍ ቶሎ ብሎ ለትዝብት ተትቷል
እንኳንም አለፈ አሮጌ ተባለ
በኛ ላይደገም አርጅቶ ተጣለ
አንኳን ተቀዳጀን አዲሱን ዘመን ቸርነትን አየን እሱ ያለውን
ዓመታችን አዲስ ዘመናችን መልካም
ልባችን የቀና የሞላብን ሰላም
ካገር ከቀያችን ከወንዝ ባህራችን
ቸር አርጎ ያቆየን ያመት ሰው ይበለን
እሱ ፈጣሪያችን
መልካም ዘመን
ዕንቁጣጣሽ
ሄለን ካሳ 2013