SBS Examines: የንግግር ነፃነታችንን ለስጋት ሳንዳርግ የተሳሳተ መረጃን መፋለም ይቻለናል?

Freedom of Speech.png

Credit: Getty / Dan Kitwood

የኦንላይን የተሳሳተ መረጃ ስርጭትን በቁጥጥር ስር የማዋል ጥሪዎች እየቀረቡ ነው። ይሁንና ይህ በንግግር ነፃነት ላይ ጥቃት እንደመፈፀም ይቆጠራል?


የተሳሳተ - እና አሳሳች መረጃ — የሐሰት መረጃ፤ ሆን ብሎ ማሰራጨት ወይም ባለማወቅ ማጋራት ከፍተኛው ሉላዊ ስጋት ተብሎ በዓለም የምጣኔ ሃብት መድረክ ተሰይሟል።

ማኅበራዊ ሚዲያም ጉዳዩን አቅላይ አልሆነም።

Uncomfortable Conversations ቀራጭና አስተናጋጅ የሆነው ጆሽ ዚፕስ “እኛ በማኅበራዊ ሚዲያ የተቀረፀና መጠነ ሰፊ አርተፊሻል ኢንተለጀንስ ታክሎበት በድንገት የኑክሊየር መረጃ የተቸረን ስልጣኔ ነን — በእሳት ላይ ነዳጅ የመጨመር ያህል” ብለዋል።

የነፃ ንግግር ተሟጋቹ ሃሳቦችን በኦንላይን ማጋራቱ የተሳሳተ መረጃ ተደርጎ አሉታዊ ትርጓሜ ሊኖረው እንደሚችል ያላቸውን ስጋት ይገልጣሉ።

“እውነታው፤ ግዙፍ፣ ዝንቅ፣ ብዝሃነት፣ መድብለ-ዘውግ ኅብረተሰብ ውስጥ የሚኖሩ ከሆነ ... ከአያሌ ሃሳቦች ጋር መታገልን ግድ ይልዎታል፤ በተወሰነ የኅብረተሰብ ስብስብ ዘንድ ዘለፋ ወይም ስድብም ሆኖ ይወሰዳል።"

"የተወሰኑቱ በተሳሳተ መረጃና አሳሳች መረጃ መካከል ሊሆኑ ይችላሉ” ሲሉ ለSBS Examines ተናግረዋል።

ወደፊት ለመራመድ የተሳሳተ መረጃና አሳሳች መረጃ ውል ያለው ትርጓሜ እንደሚያሻው የሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽነር ሎሬይን ፊንሌይ ልብ ሲያሰኙ፤

“ሁለቱንም ልንከውን ይገባል፤ ሰዎችን ከሐሰት መረጃ መጠበቅና እንዲሁም፤ በተመሳሳይ ሁኔታ ለንግግር ነፃነትም ጥበቃ ስለማድረጋችን እርግጠኞች ልንሆን ይገባናል” she said.

ይህ የ SBS Examines ክፍል፤ የንግግር ነፃነትን ሳንገድብ የተሳሳተ መረጃን መፋለም እንችላለን? ሲል ይጠይቃል።

Share
Follow SBS Amharic

Download our apps
SBS Audio
SBS On Demand

Listen to our podcasts
Independent news and stories connecting you to life in Australia and Amharic-speaking Australians.
Ease into the English language and Australian culture. We make learning English convenient, fun and practical.
Get the latest with our exclusive in-language podcasts on your favourite podcast apps.

Watch on SBS
SBS World News

SBS World News

Take a global view with Australia's most comprehensive world news service