የአውስትራሊያ ዲሞክራሲ እያሽቆለቆለ ነውን?

Australians Head To The Polls To Vote In 2019 Federal Election

Australians head to the polls to vote in 2019 Federal Election Source: Getty / James D. Morgan

የቀድሞዋ የሀገር ውስጥ ጉዳዮች (የወቅቱ የቤቶች) ሚኒስትር ክሌር ኦኒል ዲሞክራሲን በብርቅ ብሔራዊ ቅርስነት መስለውታል። የተወሰኑ ወገኖች በፊናቸው ለአደጋ ተጋልጦ ያለ ስለመሆኑ ይናገራሉ።


በቅርቡ ይፋ እንደሆነው መንግሥታዊ ሪፖርት ምልከታ፤ አመኔታ ማጣት፣ ሐሰተኛ መረጃ፣ አርተፊሻል ኢንተለጀንስ፣ ስለላና ማኅበራዊ ክፍፍሎሽ የአውስትራሊያን ዲሞክራሲ ተጋላጭ አድርገውታል።

የአውስትራሊያ የዲሞክራሲና ተጠያቂነት ተቋም ፕሮግራም ዳይሬክተር የሆኑት ቢል ብራውኒ ሲናገሩ፤

"በመላው ዓለም ዲሞክራሲ የኋልዮሽ ምለሳ ጉዳት ያገኘው መሆኑ እርግጥ ነው። በተለያዩ አገራት የዲሞክራሲ ጥራትና መስፋፋት መለኪያዎች ተሞክሮም ነገሮች የኋልዮሽ መሄዳቸውን ለማረጋገጥ ሞክሯል" ብለዋል።

ይሁንና አቶ ብራውኒ አክለው ሲያስረዱ፤ አውስትራሊያ እንዲህ ካሉቱ የከፉ ለውጦች ተመክታ እንዳለች አመላክተዋል።

ለእዚያም ለታችኛውና የላይኛው ምክር ቤቶች ምርጫ ድምፅ መስጠት ዜጋዊ ግዴታ መሆንና የገለልተኛ ኮሚሽን መኖርን በጠቀሜታነት አንስተዋል።

“እንደማስበው በመላው ዓለም የዲሞክራሲን ጥራት ለማሻሻል ከአውስትራሊያ ሥርዓትና ከአውስትራሊያ የነገሮች አከዋወን የሚቀሰሙ ትምህርቶች ይኖራሉ" ሲሉ ለ SBS Examines ጠቁመዋል።

ይህ ክፍለ ዝግጅት፤ አውስትራሊያ ውስጥ ዲሞክራሲ ምን ይመስላል? አክሎም እያሽቆለቆለ ነውን? ሲል ይጠይቃል።

Share
Follow SBS Amharic

Download our apps
SBS Audio
SBS On Demand

Listen to our podcasts
Independent news and stories connecting you to life in Australia and Amharic-speaking Australians.
Ease into the English language and Australian culture. We make learning English convenient, fun and practical.
Get the latest with our exclusive in-language podcasts on your favourite podcast apps.

Watch on SBS
SBS World News

SBS World News

Take a global view with Australia's most comprehensive world news service