ስጦታው በፍቃዱ፤ ከቤተ እምነት እስከ ማረሚያ ቤት በጎ አድራጎት

Setotaw family.jpg

Author Setotaw Befekadu and his family. Credit: S.Befekadu

ደራሲ ስጦታው በፍቃዱ በአፍላ ዕድሜያቸው ወደ አውስትራሊያ የዘለቁት ነፃ የሃይማኖት ትምህርት ዕድል አግኝተው ነው። አዘላለቃቸው ግና ያለ ቪዛ ነበር።


የእንግሊዝኛ ቋንቋ ክህሎት ማነስ አስባብ ሆኖ አውሮፕላን ማረፊያ ላይ ብልሃት እስኪዘየድ ድረስ የተግባቦት ችግር ተፈጠረ።

ከውጣ ውረዶች በኋላ ቪዛና ተቀባዮቻቸውን አገኙ።

ወደ መንፈሳዊ ኮሌጅ አመሩ።

ትምህርታቸውን ሲጨርሱ ኢትዮጵያ ውስጥ ቀይ ሽብር የተፋፋመበት ወቅት ሆነ።

ወደ አገር ቤት ከመመለስ ይልቅ አውስትራሊያ መቆየትን መረጡ።

ዘመን በዘመን ተሻረ፤ የኢትዮጵያ ሥርዓተ መንግሥታት ተለዋወጡ።

በአንድ ወቅት አንድ ስብሰባ ላይ ታድመው ሳሉ አንዲት ተናጋሪ ከመድረክ ላይ ሆነው "ድርሻን ስለመወጣት" የተናገሩት ተምሳሌያዊ ንግግር ልብና አዕምሯቸው ውስጥ ሰረፀ።

"እኔስ ለአገሬ እንደምን ነው በአቅሜ የድርሻዬን የማበረክተው?" ሲሉ እራሳቸውን ጠየቁ።

ወደ አገር ቤት ተጓዙ።

ሕይወታቸው ከማረሚያ ቤት በጎ አድራጎት አዲስ የሕይወት ምዕራፍ ጋር ተገጣጠመ።

ከአገር ቤት ወደ አውስትራሊያ እንደተመለሱ የተመለከቷቸውን ችግሮች፤ለመርዳት ያላቸውን ፍላጎት ለባለቤታቸው አስረዱ።

ባለቤታዊ ድጋፍ ተቸራቸው።

የቅርብ ወዳጆቻቸውም ታከሉ።

አንድ የአውስትራሊያ በጎ አድራጊ ቤተክርስቲያን በሥራ ፈቃድ አገዛቸው።

የኤሎሄ የማረሚያ ቤት አገልግሎታቸውን ጀመሩ።

እስካሁንም የማረሚያ ቤት አገልግሎታቸውን ከአውስትራሊያ ኢትዮጵያ እየተመላለሱ በማበርክርት ላይ ይገኛሉ።

"በችግር ያሉትን የመርዳት ኃላፊነት አለብን" ይላሉ።

የእንግሊዝኛው "From Maychew To Australia" መፅሐፋቸውም ለምረቃ ተሰናድቷል።


Share
Follow SBS Amharic

Download our apps
SBS Audio
SBS On Demand

Listen to our podcasts
Independent news and stories connecting you to life in Australia and Amharic-speaking Australians.
Ease into the English language and Australian culture. We make learning English convenient, fun and practical.
Get the latest with our exclusive in-language podcasts on your favourite podcast apps.

Watch on SBS
SBS World News

SBS World News

Take a global view with Australia's most comprehensive world news service