ምንተስኖት መንገሻ፤ለደሃ የእንግሊዝ ተማሪ ሕፃናት መርጃ በባዶ እግራቸው 160 ኪሎ ሜትሮችን የተጓዙት ኢትዮጵያዊው የኮሌጅ መምህር

Mentesnot Mengesha pic.jpg

Mentesnot Mengesha. Credit: M.Mengesha

መምህርና ደራሲ ምንተስኖት መንገሻ ነዋሪነታቸው ሎንዶን - አገረ እንግሊዝ ነው። በኒው ሲቲ ኮሌጅ የማስተማር ዘዴ መምህር ናቸው። በሃብት ቁመናዋ ከመጀመሪያው ረድፍ ላይ በምትሰለፈዋ አገረ እንግሊዝ ጣቶቻቸው ከተበጫጨቀ ጫማዎቻቸው ሾልከው ለወጡ ተማሪ ሕፃናት መርጃ የሚውል ገንዘብ እንደምን በባዶ እግራቸው ተጉዘው እንዳሰባሰቡ ይናገራሉ። ለአገራቸው ለኢትዮጵያ ተረጂዎችም በላየንስ ክለብ በኩል እርዳታ አሰባስበዋል፤ የኢትዮጵያ ቀይ መስቀል የዕድሜ ልክ አባልም ናቸው።


አንኳሮች
  • የበጎ አድራጎት ተግባርና ሽልማት
  • ድህነትና ሕፃናት በአገረ እንግሊዝ
  • የቀድሞ ግብረ ሰናይ ተግባራትና የወደፊት የረድኤት ውጥኖች
አትሳቅ አትበሉኝ

ጭጋግ መሬት ቢረግጥ

ጸሃይ ብትሸፈን፣

አየሩ ቢታፈን፣

ኑሮ ረመጥ ቢሆን፣

ዙሪያው ገባው ሁሉ

ማቅ ለብሶ ቢዳፈን፡፡

ሳቄን ማን ከልክሎኝ፣

አልፎ ሂያጂነቴን

ጉዞዬን ማን ገቶኝ፣

እርቃኔንም ብሆን

የውስጤን ነጻነት እንደያዝኩት አለሁ

በውስጤ ሃብት አለኝ፡፡

አትሳቅ አትበሉኝ ... ሳቄ  የቀረ ዕለት፣

የደኸየሁ  እንደሁ ... በፈገግታ ንፍገት፣

ያኔ ነው የኔ ሞት፡፡

ጫማም አላቂ ነው

ከስር ተሸንቁሮ፣

ልብስም ይቀደዳል

ውሉ ተተርትሮ፣

ሁሉም አላፊ ነው

ያረጃል ያፈጃል

ትናንትም አርጅቶ

ጥንት ይባላል ዱሮ፡፡

አትሳቅ አትበሉኝ  ... ሳቄ  የቀረ ዕለት

የደኸየሁ  አንደሁ ... በፈገግታ ንፍገት፣

ያኔ ነው የኔ ሞት፡፡

.............................

መታሰቢያነቱ ለጫማ አልባው ብላቴና ይሁንልኝ ... ጸደይ 2020

ምንተስኖት መንገሻ

Share
Follow SBS Amharic

Download our apps
SBS Audio
SBS On Demand

Listen to our podcasts
Independent news and stories connecting you to life in Australia and Amharic-speaking Australians.
Ease into the English language and Australian culture. We make learning English convenient, fun and practical.
Get the latest with our exclusive in-language podcasts on your favourite podcast apps.

Watch on SBS
SBS World News

SBS World News

Take a global view with Australia's most comprehensive world news service