"ከሕክምና ወደ ምክር ቤት አባልነት ለመሸጋገር አስቤያለሁ" ሰላም ፈለቀ ተገኝ

Selam Feleke tegegn II.jpg

Selam Feleke Tegegn, Multicultural Public Relations Ambassador of WA. Credit: SF.Tegegn

ሰላም ፈለቀ ተገኝ፤ ቀደም ባለው የግለ - ሕይወት ትረካዋ እንደምን ከዕድገት ቀዬዋ በቅሎ ቤት ተነስታ ከወላጆቿና ታናሽ ወንድሟ ጋር ለስደት እንደተዳረገችና ወደ አውስትራሊያ ከእነ ቤተሰቧ እንደዘለቀች አውግታለች። ቀጣይ ትረካዋ የአውስትራሊያ ምክር ቤት አባል የመሆን ትልሟ ዙሪያ ነው።


ሰላም በተለይም ባለፈው ወርሃ ሜይ 2022 የተካሔደው የአውስትራሊያ ፌዴራል ምርጫ ውስጧ ዘልቆ ገብቷል።

የፖሊሲ ቀረፃና ድንጋጌ አውጪነት ፖለቲካዊ ኃይል የሚሊዮኖችን ሕይወት ለትድግና ሊያበቃም ሆነ ለጉዳት ሊዳርግ እንደሚችል በቅርበት ተጠግታ በሌበር ፓርቲ የምርጫ ዘመቻ ቀስቃሽነት ተሳትፎዋ ወቅት ማየት ችላለች።

Bill Shorton MP (L), and Selam Tegegn (R).jpg
Bill Shorton, Minister for Government services and Minister for the NDIS (L), and Selam Feleke Tegegn (R). Credit: SF.Tegegn

በግንዛቤ ጭበጣም አልተወሰነችም። ከቶውንም ራሷን ለአውስትራሊያ የሕግ መወሰኛ ወይም የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባልነት እስከ ማብቃት ትልም ደርሳለች።

ከራሷም አልፋ ሌሎች የማኅበረሰብ አባላትም ንቁ ተሳትፎ እንዲያደርጉ ታበረታታለች።

Selam and PM Albanese.jpg
Anthony Albanese, Prime Minister of Australia (C), and Selam Feleke Tegegn (R). Credit: SF.Tegegn
'ችግር ሲደርስብን ብቻ ስንጮህ ም ማንም የሚሰማን የለም' ስትልም በዲሞክራሲያዊ ተሳትፎ ስለሚገኝ የተደማጭነትና ጉልህ ድምፅ ጠቀሜታን ታመላክታለች ።

ቁጭ ብለን ማማረር አንችልም። ተነስተን ተሳትፎ ማድረግ፣ ሌሎችንም መርዳት አለብን።
ሰላም ፈለቀ ተገኝ
ለአርአያነትም በፌዴራል ምርጫ ዘመቻ ወቅት ስለ ድምፅ አሰጣጥ ዘዴዎች፣ የምርጫ ድምፅን ግላዊና ማኅበረሰባዊ ትሩፋቶችን እንዲያስገኙ ዕጩዎችንና ፖሊሲዎቻቸውን ለይቶ ስለማወቅ በማኅበራዊ ሚዲያ ገፆችዋ አስፍራ ግንዛቤ ለማስጨበጥ ጥራለች ።

ሰላም በጋራ ለማደግ የአንድነትና ተሳትፎ ጠቀሜታን አፅንዖት ሰጥታ ታሳስባለች።

ሁላችንም በያለንበት ተለያይተን እንዴት ነው የምናድገው?
ከአንድነትና ትብብር ይልቅ የቅናት መንፈስን ማንገስ ወደፊት አራማጅ እንዳልሆነም ልብ ታሰኛለች።

'ሕዝባችን እንዲሳተፍ እፈልጋለሁ። መንግሥት እንድንሳተፍ ይፈልጋል። ያለ ተሳትፎ ለውጥ አይመጣም፣ ስትልም ታበረታታለች።

Share
Follow SBS Amharic

Download our apps
SBS Audio
SBS On Demand

Listen to our podcasts
Independent news and stories connecting you to life in Australia and Amharic-speaking Australians.
Ease into the English language and Australian culture. We make learning English convenient, fun and practical.
Get the latest with our exclusive in-language podcasts on your favourite podcast apps.

Watch on SBS
SBS World News

SBS World News

Take a global view with Australia's most comprehensive world news service