በሊብራል ፓርቲና እንደ ተቃዋሚ ቡድን መሪነቴ መልካም የኢትዮጵያ አዲስ ዓመትን እመኝላችኋለሁ።
ለአውስትራሊያውያን - ኢትዮጵያውያን ማኅበረሰብ፣
አውስትራሊያ ውስጥ የትም ሁኑ የት፤ አዲሱን ዓመት ዘላቂ ሥርዓተ ወጎች በሆኑት በፀሎት፣ ከቤተሰብ በመጣ መልዕክት፣ ከወዳጆች ጋር ሆኖ በማክበር፣ ችቦ በመለኮስ፣ ምናልባትም አረቄ በመጎንጨት ትቀበሉታላችሁ።
ምንም ጥርጣሬ የለውም፤ ስለ ዕንቁጣጣሽ አመጣጥ አፈ ታሪክ መነገሩም አይቀርም።
ንግሥተ ሳባ ንጉሥ ሰለሞንን ጎብኝታ ወደ አገር ቤት ስትመለስ እንደምን ዕንቁ ይዛ እንደመጣች።
ንግሥቲቱ በጉዞዋ እንደከበረች ሁሉ፤ አውስትራሊያም እዚህች ታላቅ አገራችን ላይ በፍልሰትም ይሁን በስደተኝነት በሠፈሩት ኢትዮጵያውያን ከብራለች።
ከ1960ዎቹ ወዲህ በበርካታ ምክንያቶች ወደ አውስትራሊያ መጥተዋል።
ከጭቆና ለመሸሽ፣ የተፈጥሮ አደጋን ለማምለጥ፣ መልካም ዕድሎችን ፍለጋና ከቤተሰብ ጋር ለመቀላቀል።
ምክንያቶቹ ምንም ይሁኑ ምን፤ ምድራችንን የረገጡ ኢትዮጵያውያን ታትረው ሠረተዋል፤ የአውስትራሊያን የሕይወት ዘዬ ተቀብለዋል፣ እንዲሁም፤ እንደ አገር አዋድዶ ያያያዙንን ዲሞክራሲያዊ ዕሴቶች በእጅጉ ተከባክበው ይዘዋል።
ንግሥቲቱ [ንግሥተ ሳባ] በጉዞዋ እንደከበረች ሁሉ፤ አውስትራሊያም እዚህች ታላቅ አገራችን ላይ በፍልሰትም ይሁን በስደተኝነት በሠፈሩት ኢትዮጵያውያን ከብራለች።የተቃዋሚ ቡድን መሪ ፒተር ዳተን
14 ሺህ ያህል የኢትዮጵያውያን ማኅበረሰብ አባላት በየዓመቱ ለሕብረተሰባችን ሁነኛ አስተዋፅዖዎችን ያበረክታሉ።
እያንዳንዳቸውን ስለ አይበገሬነታቸውና አበርክቶዎቻቸው አመሰግናለሁ።
የኢትዮጵያ አዲስ ዓመት የተሃድሶና ተስፋ ዘመን ነው።
እናም፤ ለአውስትራሊያውያን - ኢትዮጵያውያን በመጪው አዲስ ዓመት መልካም ዕድሎችንና ጤናን እመኛለሁ።
መልካም አዲስ ዓመት
በጣም አመሰግናለሁ።