አንኳሮች
- የድርድር ግቦች
- የስኬት ትሩፋቶች
- የክሽፈት መዘዞች
“ድርድሩ ከተሳካ በየትኛውም ወገን ላለ ሰው የሕይወትም የመንፈስም ትሩፋት ይኖረዋል፤ ካልተሳካ ማንም ተጠቃሚ አይሆንም። ምናልባትም የሚያተርፍ ቢኖር የኢትዮጵያን መውደቅ አሰፍስፈው ለሚጠብቁ ይሆናል።” ወ/ሮ ሰብለወርቅ አሰፋ
***
“ድርድሩ ካልተሳካ የምንመለሰው ወደ ጦርነት ነው። ተሳክቶ መፍትሔ ካገኘን ጦርነትና ውድመትን ያስቀርልናል።” አቶ ዳባሳ ዋቅጅራ
***
“ድርድሩ እንዲሳካ የሚያደርጉ በርካታ ጉዳዮች አሉ። ድርድሩ የግድ መሳካት እንደሚኖርበት አስገዳጅ ሁኔታዎች አሉ። ያለውን ችግር በድርድር የመፍታት አማራጭ የሌለው ጉዳይ ነው። እንዲያም ሆኖ ድርድሩ ሳይሳካ ቢቀር እንደ ዳርፎርና ሶማሊያ ነው የምንሆነው።” ዶ/ር ተበጀ ሞላ