አንኳሮች
- ብሔራዊ ጥቅምና የሰላም ተደራዳሪዎች
- ለሰላም ስኬት ሕዝባዊ ተፅዕኖዎች
- የባሕር ማዶ ነዋሪ ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያን ሚና
“ሁልጊዜ ጦርነትን የሚጀምሩት ፖለቲከኞችና የጦር ጠበብቶች ናቸው። ሕዝብ እንደ ሕዝብ ሰላምን ይፈልጋል። ለሰላም የሚደረገው ማንኛውም ርብርብ በሁሉም ወገን ድጋፍ ሊደረግለት ይገባል። በዳያስፖራውም ጭምር፤ ነገር ግን የሰላም ንግግሩ እውነተኛ መሆንና ሕዝብን ያቀፈ መሆን አለበት።” አቶ ልዑል ፍሰሃ
***
“ችግሩን ከምናባብሰው አካል አንዱ ስለሆንን፤ ችግሩ እንዲበርድም ለማድረግ በውጭ የምንንኖር ኢትዮጵያውያን በሙሉ ሚና ሊሆን ይገባል። ይኼ ድርድር ውጤታማ እንዲሆን እያመመንም ጭምር አሉታዊ ነገሮችን ባለማራገብ፤ ከልዩነቶቻችን ይልቅ አንድነታችን ላይ መሥራት የምንችልበት ዕድል ቢኖር ኢትዮጵያ አትራፊ ትሆናለች።” ወ/ሮ ሰብለወርቅ ታደሰ
***
“ያለፉ አሉታዊ ነገሮች ላይ ከማተኮር ይልቅ የሚመጣው ተስፋ ላይ ከተተኮረ ችግሩ ይፈታል ብዬ አስባለሁ። ሁሉም የሰላም አምባሳደር ከሆነ የጦርነት ድምፆች ይቀንሳሉ። የሰላም መንገዶች ይጨምራሉ ብዬ አስባለሁ።” አቶ ዳባሳ ዋቅጅራ
***
"ከተቻለ ገንቢ ምክረ ሃሳብ ማቅረብ፤ ካልተቻለ አላስፈላጊ ተፅዕኖ ፈጥሮ ውይይቱ ዕንቅፋት እንዳይገጥመው ማድረግ።" ዶ/ር ተበጀ ሞላ