አንኳሮች
- የሰላም ድርድርና የኢትዮጵያ አገራዊ ምክክር ኮሚሽን
- ልምድ ቀሰማ
- አዎንታዊና አሉታዊ ተፅዕኖዎች
“አሁን ኢትዮጵያ ውስጥ ያለው መንግሥት የደካማ ኃይሎች ስብስብ ስለሆነ የኢትዮጵያ አገራዊ ምክክር ኮሚሽን ፈርጥ የሆነ ጥሩ ሃሳብ ቢያቀርብላቸውም የመወሰን አቅማቸው ውስን ነው።” አቶ ልዑል ፍሰሃ
***
“በኢትዮጵያና መንግሥትና ሕወሓት መካከል የሚካሔደው ድርድር በሰላም ቢያልቅ ለኢትዮጵያ አገራዊ ምክክር ኮሚሽኑ ትልቅ ግብኣት ይሆናል። አገራዊ ምክክሩ ሁላችንም ሰጥተን የምንቀበልበት መደረክ ነው፤ ድርድሩ ካልተሳካ በአገራዊ ምክክሩ ላይ ጥላ ያጠላል ብዬ ነው የማስበው።” ወ/ሮ ሰብለወርቅ ታደሰ
***
“ድርድሩ ከተሳካ በሰላማዊ መንገድ ተወያይተን ችግሮችን መፍታት እንድንችል ትምህርት ይሰጠናል፤ ለአገራዊ ምክክር ኮሚሽኑ ዕድል ይከፍታል ብዬ አስባለሁ። ኦሮሚያ ውስጥ ጠብመንጃ አንስቶ የሚዋጋ ስላለ ከእነዚያም ጋር ከጠብመንጃ ይልቅ በሰላማዊ መንገድ ተነጋግሮ ወደ አገራዊ ጉዳይ የማምጣትና አብሮ የመሥራት ዕድል ይፈጥራል ። በአገራዊ ምክክሩ የመሳተፍ ዕድልም ይጨምራል።” አቶ ዳባሳ ዋቅጅራ
***