አንኳሮች
- አደራዳሪዎች
- ገለልተኛነት
- ተቀባይነት
“ምዕራባውያን በተለይ በአገራችን ጉዳይ እጃቸውን በግልፅ እያስገቡ ነው ያሉት። እነሱ ያጣሉናል፤ እነሱ ልናስታርቃችሁ እንምጣ ይላሉ። መፍትሔ የሚሆነው እሱ አይደለም። መፍትሔ የሚሆነው ባለፉት 20 ወራት በሕዝባችን ላይ የደረሰውን ግፍ፣ ሰቆቃና የኢኮኖሚ ውድቀት ተረድተን ከዚህ በኋላ ቢያንስ ያ ነገር እንዳይቀጥል ተመሳሳይ አቋም ልንይዝ ይገባል።” አቶ ልዑል ፍሰሃ
***
“ባለፉት 20 ወራት ብቻ ሳይሆን ለ30 ዓመታት ኢትዮጵያ በታሪኳ ሆኖባት በማያውቀው መልኩ መፈንጫ ነበረች ብዬ ነው የማስበው። እስካሁኗ ደቂቃ ድረስ። ይካሔዳል ለሚባለው ድርድር ቢያንስ አደራዳሪዎቹ ከነጮቹ ይልቅ አፍሪካውያን መሆናቸው የተሻለ ሊሆን ይችላል” ወ/ሮ ሰብለወርቅ ታደሰ
***
“አደራዳሪዎቹ ምን ይሁኑ ምን ሁለቱ አካላት ከተቀበሏቸው ብዙም አስቸጋሪ ይሆናል ብዬ አላስብም። ዋናው አደራዳሪዎቹ ብቃት ያላቸው፣ ገለልተኛና የጥቅም ግጭት የሌላቸው መሆኑ ነው።” አቶ ዳባሳ ዋቅጅራ
***
“አደራዳሪዎቹ ምን ይሁኑ ምን ሁለቱ አካላት ከተቀበሏቸው ብዙም አስቸጋሪ ይሆናል ብዬ አላስብም። ዋናው አደራዳሪዎቹ ብቃት ያላቸው፣ ገለልተኛና የጥቅም ግጭት የሌላቸው መሆኑ ነው።” አቶ ዳባሳ ዋቅጅራ
***
“ዋናው ቁልፉ ጥያቄ መሆን ያለበት ሁሉም ወገኖች በኢትዮጵያዊነትና በአገሪቱ ህልውና ላይ ያምናሉ ወይ ነው።” ዶ/ር ተበጀ ሞላ