አንኳሮች
- መደበኛ መሠረታዊ አገልግሎቶች አቅርቦት ለትግራይ
- የክልልና ፌዴራል አስተዳደር በትግራይ
- ጥርጣሬና አመኔታ
“ስጋቶቻችንን ይፋ እናድርግ። እንተማመን። ሁላችንም በዚህ ግፊት ውስጥ ከሄድን ውጤታማ አንሆንም። ውጤታማ የምንሆነው አንድ የጋራ አገር ይኑረን ብለን ዳግም ልብ የሚያደማ ነገር ውስጥ እንዳንገባ ከተማመን፣ ትዕቢታችንንና አልነካ ባይነታችንን ለጋራ ሰላም ስንል ስናስካ ብቻ ነው።” ወ/ሮ ሰብለወርቅ አሰፋ
***
“የትግራይ ሕዝብ የኢትዮጵያ ሕዝብ አካል ነው። በትግራይ ሕዝብ ላይ የሚደርስ በደል የሁላችንም ጥያቄ መሆን አለበት።” ዶ/ር ተበጀ ሞላ
***
“የትግራይ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ለፌዴራሉ መንግሥት ዕውቅናን መስጠት አለበት፤ የፌዴራል መንግሥቱ ለትግራይ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ዕውቅናን መስጠት አለበት። ዕውቅና ካልተሰጣጡ ድርድሩ ዋጋ የለውም።” አቶ ልዑል ፍሰሃ